ኢያሱ 9:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይላቸውን በአንድነት አስተባብረው በኢያሱና በእስራኤላውያን ላይ ለመዝመት መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱንና እስራኤልን ለመውጋት በአንድነት መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱንና እስራኤልን ሁሉ ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ። |
እነዚህ የኢየሩሳሌም፥ የኬብሮን፥ የያርሙት፥ የላኪሽና የዔግሎን ገዢዎች አምስቱ አሞራውያን ነገሥታት ሠራዊታቸውን አስተባብረው፥ የጦር ግንባር በመፍጠር፥ ገባዖንን ከበው አደጋ ጣሉባት።
እናንተም የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራችሁ ወደ ኢያሪኮ መጣችሁ፤ የኢያሪኮም ሰዎች፥ እንዲሁም አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን እናንተን ለመውጋት ተነሡ፤ እኔ ግን በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጀኋችሁ።
እነርሱ ተአምራት የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ እነዚህ መናፍስት ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት ሰዎችን ለመሰብሰብ ወደ ዓለም ነገሥታት ሁሉ ይሄዳሉ።