ነገር ግን ዳዊትና ዮናታን እርስ በርሳቸው በገቡት የተቀደሰ ቃል ኪዳን ምክንያት ዳዊት የሳኦልን የልጅ ልጅ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን አሳልፎ አልሰጣቸውም።
ኢያሱ 9:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕዝቡ መሪዎች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ምለውላቸው ስለ ነበረ እስራኤላውያን እነርሱን አልገደሉአቸውም። ስለዚሁም ጉዳይ እስራኤላውያን ሁሉ በመሪዎቻቸው ላይ አጒረመረሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም እስራኤላውያን አልወጓቸውም፤ የጉባኤው መሪዎች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ምለውላቸው ነበርና። ማኅበሩም ሁሉ በመሪዎቹ ላይ አጕረመረሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በጌታ ስለ ማሉላቸው የእስራኤል ልጆች አልመቱአቸውም። ማኅበሩም ሁሉ በአለቆቹ ላይ አጉረመረሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማኅበሩም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስለ ማሉላቸው የእስራኤል ልጆች አልገደሉአቸውም። ማኅበሩም ሁሉ በአለቆቹ ላይ አጕረመረሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስለ ማሉላቸው የእስራኤል ልጆች አልመቱአቸውም። ማኅበሩም ሁሉ በአለቆቹ ላይ አጉረመረሙ። |
ነገር ግን ዳዊትና ዮናታን እርስ በርሳቸው በገቡት የተቀደሰ ቃል ኪዳን ምክንያት ዳዊት የሳኦልን የልጅ ልጅ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን አሳልፎ አልሰጣቸውም።
ከመናገርህ በፊት አስብ፤ ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ለመስጠት በችኰላ ስእለት አታድርግ፤ እግዚአብሔር በሰማይ አንተ ግን በምድር መሆንህን በማሰብ የምትናገረው ቃል የተመጠነ ይሁን።
ወደ ኃጢአት እንዳይመራህ ለአንደበትህ ከገደብ ያለፈ ነጻነት አትስጠው፤ በዚህ ዐይነት “ይህን የተናገርኩት ሳላውቅ ነው” ብለህ በእግዚአብሔር አገልጋይ ፊት ይቅርታ ከመጠየቅ ትድናለህ፤ አለበለዚያ ግን የደከምክበትን ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቊጣ በገዛ እጅህ እንደ መጋበዝ ይሆንብሃል።
ምንም ዐይነት ልዩነት ሳይደረግ ለጻድቅና ለኃጢአተኛ ለደግና ለክፉ፥ ለንጹሓንና ንጹሓን ላልሆኑ መሥዋዕት ለሚያቀርቡትና ለማያቀርቡትም የሚገጥማቸው ዕድል አንድ ዐይነት ነው፤ ይኸውም ደጉ ሰው ከኃጢአተኛው የተሻለ ዕድል የለውም፤ መሐላን የሚፈራው መሐላን ከሚደፍረው ሰው ተለይቶ አይታይም።
ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጒዞ ጀምረው ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሕዝብ ወደሚኖሩባቸው ከተሞች ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ በኤሮትና ቂርያትይዓሪም ተብለው ይጠሩ ነበር፤
መሪዎቹ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ገብተንላቸዋል፤ ስለዚህም አሁን ጒዳት ልናደርስባቸው አይገባም፤