ጊዜውም ገና ሌሊት ነበር፤ ንጉሡ ግን ከመኝታው ተነሥቶ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖች እንዲህ አላቸው፤ “የሶርያውያንን ዕቅድ ልንገራችሁ! እነርሱ በዚህ ስላለው ራብ ያውቃሉ፤ ስለዚህ ሰፈራቸውን ለቀው በገጠር ለመሸሸግ ሄደዋል፤ እኛም ምግብ ፍለጋ ብንወጣ ከነሕይወታችን ማርከው ከተማችንን ይወስዳሉ።”
ኢያሱ 8:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው፦ “ከከተማይቱ በስተኋላ አድፍጣችሁ ቈዩ፤ ይሁን እንጂ ከከተማይቱ ብዙ ሳትርቁ አደጋ ለመጣል በሚያስችላችሁ ሁኔታ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ የሚል ትእዛዝም ሰጣቸው፤ “እነሆ፤ ከከተማዪቱ በስተጀርባ ታደፍጣላችሁ፤ ከከተማዪቱ አትራቁ፤ ሁላችሁም ነቅታችሁ ተጠባበቁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “እነሆ፥ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ተደበቁ፤ ከከተማይቱ አትራቁ፥ ሁላችሁም ነቅታችሁ ጠብቁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “እነሆ፥ ሂዱና ከከተማዪቱ በስተኋላ ተደበቁ፤ ከከተማዪቱ አትራቁ፤ ሁላችሁም ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ እነሆ፥ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ተደበቁ፥ ከከተማይቱ አትራቁ፥ ሁላችሁም ተዘጋጁ፥ |
ጊዜውም ገና ሌሊት ነበር፤ ንጉሡ ግን ከመኝታው ተነሥቶ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖች እንዲህ አላቸው፤ “የሶርያውያንን ዕቅድ ልንገራችሁ! እነርሱ በዚህ ስላለው ራብ ያውቃሉ፤ ስለዚህ ሰፈራቸውን ለቀው በገጠር ለመሸሸግ ሄደዋል፤ እኛም ምግብ ፍለጋ ብንወጣ ከነሕይወታችን ማርከው ከተማችንን ይወስዳሉ።”
በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከሠራዊቱ ከፊሉን ከይሁዳ ሠራዊት በስተጀርባ በማድፈጥ፥ አደጋ እንዲጥሉ ሲልክ፥ የቀሩትን ደግሞ የይሁዳን ሠራዊት ፊት ለፊት እንዲገጥሙአቸው አደረገ።
ነገር ግን እሺ አትበላቸው፤ እርሱን ሳንገድል እህል አንበላም፤ ውሃም አንጠጣም በማለት የተማማሉ ከአርባ የሚበልጡ ሰዎች እርሱን ለመግደል አድፍጠዋል፤ አሁን እነርሱ የሚጠብቁት የአንተን መልስ ብቻ ነው።”
በዚህም ጊዜ ብንያማውያን መሸነፋቸውን ተገነዘቡ። ይህም የሆነበት ምክንያት እስራኤላውያን በጊብዓ አካባቢ አስፍረዋቸው በነበሩ የሽምቅ ወታደሮች በመተማመን ወደ ኋላ አፈግፍገው ስለ ነበረ ነው።
የሴኬም ኗሪዎች በአቤሜሌክ ላይ በጠላትነት ተነሥተው ጥቂት ሰዎችን መርጠው በተራሮች ጫፍ ላይ ሸመቁ፤ በመንገዳቸው የሚያልፈውን ሰው ሁሉ ዘረፉ፤ አቤሜሌክም ይህን ሁሉ ሰማ።
እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ እየተቃወሙ አስቸግረዋቸው ስለ ነበረ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አማሌቃውያንን ለመቅጣት ወስኖአል።