ኢያሱ 8:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከተማይቱም ሰዎች እርስ በርስ በመጠራራት በሙሉ ወጥተው እነርሱን ማሳደድ ቀጠሉ፤ ኢያሱንም በሚያሳድዱበት ጊዜ ከከተማይቱ እየራቁ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋይ ሰዎች በሙሉ እንዲያሳድዷቸው ተጠሩ፤ ኢያሱንም አሳደዱት፤ በዚህ ሁኔታም የጋይ ሰዎች ከከተማዪቱ እንዲርቁ ተደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከተማይቱም የነበሩ ሰዎች ሁሉ እነርሱን እዲያሳድዱአቸው ተጠሩ፤ ኢያሱንም አሳደዱት፥ ከከተማይቱም እንዲርቁ አደረጓቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሀገሪቱም ሰዎች ሁሉ ተጠሩ፤ የእስራኤልንም ልጆች ተከትለው አሳደዱአቸው፤ ከከተማዪቱም እንዲርቁ አደረጓቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከተማይቱም የነበሩ ሰዎች ሁሉ ሊያሳድዱአቸው ተጠሩ፥ ኢያሱንም አሳደዱት፥ ከከተማይቱም እንዲርቁ አደረጓቸው። |
እነርሱ ተአምራት የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ እነዚህ መናፍስት ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት ሰዎችን ለመሰብሰብ ወደ ዓለም ነገሥታት ሁሉ ይሄዳሉ።
ብንያማውያን ሠራዊቱን እየተከተሉ በወጡ ጊዜ ከከተማው ርቀው ሄዱ፤ በዋናው መንገድ ላይ እንደበፊቱ በሠራዊቱ ላይ አደጋ መጣል ጀመሩ፤ ወደ ቤትኤልና ወደ ጊብዓ በሚወስዱት መንገዶችና በሜዳው ላይ ሠላሳ እስራኤላውያንን ገደሉ።