ኢያሱ 6:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም በሁለተኛው ቀን ከተማይቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመለሱ፤ እስከ ስድስት ቀንም በዚሁ ዐይነት አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁለተኛውም ቀን ከተማዪቱን አንድ ጊዜ ከዞሩ በኋላ ወደ ሰፈር ተመለሱ፤ ስድስት ቀን ሙሉም እንዲሁ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁለተኛውም ቀን ከተማይቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመለሱ፤ ስድስት ቀንም እንዲህ አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁለተኛውም ቀን የቀረው ሕዝብ ሁሉ ከተማዪቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመለሱ፤ ስድስት ቀንም እንዲህ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሁለተኛውም ቀን ከተማይቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመለሱ፥ ስድስት ቀንም እንዲህ አደረጉ። |
ሰባቱን እምቢልታ የያዙት ሰባት ካህናት እምቢልታቸውን ሳያቋርጡ እየነፉ ከእግዚአብሔር ታቦት ፊት ለፊት ሄዱ፤ መለከቱ ሳያቋርጥ እየተነፋ ወታደሮቹ ከካህናቱ ቀድመው ሌላው ሕዝብ ደግሞ ከታቦቱ በኋላ ይከተል ነበር።
በሰባተኛው ቀን ጎሕ ሲቀድ ማልደው ተነሥተው በዚሁ ተመሳሳይ ሁኔታ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዞሩአት፤ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ የዞሩበት ቀን ይህ ብቻ ነበር።