በዚህም ዐይነት ሕዝብህ ለቀድሞ አባቶቻችን ርስት አድርገህ በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለአንተ ታዛዦች እንዲሆኑና እንዲያከብሩህ አድርግ።
ኢያሱ 4:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ምክንያት በምድር ላይ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ እንደ ሆነ ይገነዘባል፤ እናንተም አምላካችሁ እግዚአብሔርን ለዘለዓለም ታከብራላችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ያደረገውም፣ የእግዚአብሔር ክንድ ብርቱ መሆኑን የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንዲያውቁና እናንተም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለዘላለም እንድትፈሩ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይኸውም የጌታ እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ፥ አምላካችሁንም ጌታን ለዘለዓለሙ እንድትፈሩ ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም የእግዚአብሔር ኀይል ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ፥ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን በሥራው ሁሉ እንድትፈሩ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይኸውም የእግዚአብሔር እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ፥ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ለዘላለሙ እንድትፈሩ ነው። |
በዚህም ዐይነት ሕዝብህ ለቀድሞ አባቶቻችን ርስት አድርገህ በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለአንተ ታዛዦች እንዲሆኑና እንዲያከብሩህ አድርግ።
ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው።
ብልጽግናና ክብር ሁሉ የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተ ሁሉን ትገዛለህ፤ ኀይልና ብርታት ያንተ ናቸው፤ የወደድከውንም ታላቅና ብርቱ ማድረግ ይቻልሃል።
እግዚአብሔር በእንዴት ያለ ታላቅ ኀይል ግብጻውያንን እንዳሸነፈ እስራኤላውያን ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርና በአገልጋዩ በሙሴ አመኑ።
አምላክ ሆይ፥ ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ የተቤዠኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ በሥልጣንህ እንደ ድንጋይ ጸጥ አሉ።
ሙሴም “አይዞአችሁ፥ አትፍሩ፤ እግዚአብሔር በዚህ ሁኔታ ወደ እናንተ የመጣው ሊፈትናችሁና እርሱን በመፍራት ኃጢአት ከመሥራት ርቃችሁ እንድትኖሩ ነው” ሲል መለሰላቸው።
ከእነርሱ ጋር የዘለዓለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መልካም ነገር ከማድረግም አላቋርጥም፤ በእውነት እንዲፈሩኝ አደርጋለሁ። ከዚያም በኋላ ፊታቸውን ከእኔ ወደ ሌላ አይመልሱም።
በዚያች ምድር ለረጅም ዘመናት መኖር እንድትችሉ አንተና ልጆችህ፥ የልጅ ልጆችህም በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን መፍራትና እኔ ለሰጠኋችሁ ደንቦችና ትእዛዞች ታዛዦች መሆን ይገባችኋል።
በዚህች ቀን እግዚአብሔር በአንተ ላይ ድልን ያጐናጽፈኛል፤ እኔም ራስህን እቈርጣለሁ፤ የፍልስጥኤማውያንንም ወታደሮች ሥጋ ለአሞራዎችና ለአራዊት ምግብ አድርጌ እሰጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ መላው ዓለም በእስራኤል ዘንድ አምላክ እንዳለ ያውቃል።