La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 24:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ አሰናበተ፤ እያንዳንዱም ወደየርስት ይዞታው ተመልሶ ሄደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ ወደየርስቱ እንዲሄድ አሰናበተ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱም እያንዳንዱን ሰው ሕዝቡን ወደ ርስቱ እዲሄድ አደረገ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን አሰ​ና​በተ፤ ሁሉም ወደ​የ​ቦ​ታ​ቸው ገቡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱም ሕዝቡን በእያንዳንዱ ወደ ርስቱ ሰደደ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 24:28
7 Referencias Cruzadas  

በተረፈ ሌሎቹ እስራኤላውያን፥ ካህናትና ሌዋውያን በየርስታቸው በሌሎቹ የይሁዳ ከተሞችና መንደሮች ይኖሩ ነበር።


በዚህ ዐይነት የማንኛውም እስራኤላዊ ርስት ወደ ሌላ ነገድ አይተላለፍም፤ ከገዛ ነገዱ ጋር የተያያዘ ይሆናል፤


ስለዚህ ያም ርስት ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ ሊተላለፍ አይቻልም፤ እያንዳንዱ ነገድ የራሱን ርስት እንደ ያዘ ይኖራል።


ኢያሱም ባርኮ አሰናበታቸውና ወደ ሰፈራቸው ሄዱ፤


ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የነገረንን ቃል ሁሉ ስለ ሰማ ይህ ድንጋይ በእኛ ላይ ምስክር ነው፤ ስለዚህም አምላካችሁን ብትክዱ በእናንተ ላይ ምስክር ይሆንባችኋል።”


ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ በአንድ መቶ ዐሥር ዓመት ዕድሜው ሞተ።


ኢያሱ ሕዝቡን ባሰናበተ ጊዜ እስራኤላውያን ሁሉ የየራሳቸውን ድርሻ ለመያዝ ወደየተመደበላቸው ርስት ሄዱ።