ከንፍታሌም ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው ሦስት ከተሞች በገሊላ ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ቄዴሽ፥ ሐሞት፥ ዶርና ቃርታን ናቸው።
ኢያሱ 21:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጌርሾን ጐሣ በሙሉ በድምሩ ዐሥራ ሦስት ከተሞችን ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ተረከቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጌርሶናውያን ጐሣዎች የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ከነመሰማሪያዎቻቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው ዐሥራ ሦስት ከተሞች ከመሰማሪያቸው ጋር ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው ዐሥራ ሦስት ከተሞች ከመሰማርያቸው ጋር ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው አሥራ ሦስት ከተሞች ከመሰምርያቸው ጋር ናቸው። |
ከንፍታሌም ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው ሦስት ከተሞች በገሊላ ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ቄዴሽ፥ ሐሞት፥ ዶርና ቃርታን ናቸው።