አሜስያስ ግን የዮአስን መልስ ከምንም አልቈጠረውም፤ ስለዚህም ንጉሥ ዮአስ ሠራዊቱን አስከትሎ በአሜስያስ ላይ በመዝመት በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤትሼሜሽ ጦርነት ገጠመው፤
ኢያሱ 19:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይርኦን፥ ሚግዳልኤል፥ ሖሬም፥ ቤትዐናትና ቤትሼሜሽ ተብለው የሚጠሩ ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞች በዙሪያቸው ታናናሽ ከተሞች ጋር በዚህ ክልል ውስጥ ይገኛሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይርኦን፣ ሚግዳልኤል፣ ሖሬም፣ ቤትዓናትና ቤትሳሚስ። እነዚህ ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይርኦን፥ ሚግዳል-ኤል፥ ሖሬም፥ ቤት-ዓናት፥ ቤት-ሳሚስ፤ ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቄሮህ፥ ሚጋላህሪም፥ ቤታሚና፥ ቴስሚስ፤ ዐሥራ ዘጠኝ መንደሮችና ከተሞቻቸው። |
አሜስያስ ግን የዮአስን መልስ ከምንም አልቈጠረውም፤ ስለዚህም ንጉሥ ዮአስ ሠራዊቱን አስከትሎ በአሜስያስ ላይ በመዝመት በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤትሼሜሽ ጦርነት ገጠመው፤
ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል።
ድንበሩም መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ሆኖ፥ ከታቦር፥ ከሻሐጹማና ከቤትሼሜሽ ጋር ይዋሰናል፤ እርሱም ዐሥራ ስድስት ከተሞችንና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ሁሉ ያጠቃልላል፤
የንፍታሌም ነገድ በቤትሼሜሽና በቤትዓናት ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች አላስወጡም፤ ስለዚህም የንፍታሌም ሕዝብ ከከነዓናውያን ጋር እዚያው አብረው መኖርን ቀጠሉ፤ ሆኖም የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ከነዓናውያንን ያስገድዱአቸው ነበር።