ሰሎሞንን “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ ከተሞች ለካ እነዚህ ናቸውን?” አለው፤ በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ ያ አካባቢ በሙሉ ካቡል እየተባለ ይጠራል፤
ኢያሱ 19:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ምሥራቅም ይታጠፍና ድንበሩ ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ነዒኤል በሚወስደው መንገድ ከዛብሎንና ከይፍታሕኤል ሸለቆ እየተዋሰነ ወደ ቤትዳጎን ይዘልቃል። በሰሜንም ወደ ካቡል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ቤትዳጎን ይመለስና ዛብሎንንና የይፍታሕኤልን ሸለቆ ይዞ፣ ካቡልን በስተግራ በመተው በሰሜን በኩል ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ንዒኤል ያቀናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤትዳጎን ዞረ፥ ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤት-ዔሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ሰሜን ወደ ካቡል ወጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ቤቴጌነት ይዞራል፤ በመስዕም በኩል ከዛብሎንና ከጋይ ከይፍታሕኤል ይያያዛል ወደ ሳፍቱ ቤታሜሕና ወደ ኢንሂል ይደርሳል፤ ወደ ኮባ ማሾሜልም ያልፋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤትዳጎን ዞረ፥ ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፥ በስተ ግራ በኩልም ወደ ካቡል ወጣ፥ |
ሰሎሞንን “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ ከተሞች ለካ እነዚህ ናቸውን?” አለው፤ በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ ያ አካባቢ በሙሉ ካቡል እየተባለ ይጠራል፤
ገዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማና ማቄዳ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል።