ኢያሱ 18:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹም የምድሪቱን ሁኔታ ለማጥናት ከመሄዳቸው በፊት ኢያሱ፥ “ወደ ምድሪቱ ሁሉ ሂዱ፤ አቀማመጥዋንም አጥንታችሁ መዝግቡ፤ ወደ እኔም ተመልሳችሁ ኑ፤ እኔም በዚህ በሴሎ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ዕጣ እጥልላችኋለሁ” የሚል መመሪያ ሰጣቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹ የምድሪቱን ሁኔታ ለማጥናትና ለመመዝገብ ጕዞ ሲጀምሩ ኢያሱ፣ “ሄዳችሁ የምድሪቱን ሁኔታ አጥኑና በዝርዝር ከጻፋችሁ በኋላ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም እዚሁ ሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ እጥልላችኋለሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎቹም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ተመልክተው ሊጽፉ የሄዱትን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ሂዱ፥ ምድሩንም ዞራችሁ እዩና ጻፉት፥ ወደ እኔም ተመለሱ፤ በዚህም በሴሎ በጌታ ፊት ዕጣ እጥልላችኋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን፥ “ሂዱ፤ ምድሩንም ዞራችሁ ጻፉት፤ ወደ እኔም ተመለሱ፤ በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ” ብሎ አዘዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፥ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን፦ ሂዱ፥ ምድሩንም ዞራችሁ ጻፉት፥ ወደ እኔም ተመለሱ፥ በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ ብሎ አዘዛቸው። |
ሰዎቹም በአገሪቱ በመላ ተዘዋወሩ፤ ከተሞቹንም ሁሉ መዝግበው ምድሪቱ ለሰባት ነገድ እንዴት እንደምትከፈል በጽሑፍ ገለጡ፤ ከዚህም በኋላ ኢያሱ ወዳለበት ወደ ሴሎ ተመልሰው መጡ፤
ሳኦልም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ! ዛሬ ስለምን መልስ አልሰጠኸኝም? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! በእነዚህ በተቀደሱ ድንጋዮች አማካይነት መልስ ስጠኝ፤ ይህን በደል የሠራነው ዮናታን ወይም እኔ ከሆንን በኡሪም አማካይነት፥ ይህን በደል የፈጸሙ ሕዝብህ እስራኤል ከሆኑ በቱሚም አማካይነት መልስ ስጠኝ።” መልሱም ዮናታንንና ሳኦልን ስላመለከተ ሕዝቡ ነጻ ሆኑ፤