ኢያሱ 18:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፋርዐሞናይ፥ ዖፍኒና፥ ጌባዕ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ ሁለት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙ ትናንሽ ከተሞችንም መንደሮችንም ይጨምራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፊርዓሞናይ፣ ዖፍኒ እንዲሁም ጌባዕ ናቸው፤ እነዚህም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፊርዓሞናይ፥ ዖፍኒ፥ ጋባ፤ ዐሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃራፋ፥ ቄፍራ፥ ሞኒ፥ ጋባህ፤ ዐሥራ ሁለቱ ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ከዚህም በኋላ ንጉሥ አሳ፥ ባዕሻ ራማን ለመመሸግ አከማችቶት የነበረውን ድንጋይና እንጨት ከዚያ ለማንሣት እንዲረዳው ሕዝቡ አንድም ሳይቀር እንዲመጣ ወደ ይሁዳ ግዛቶች ሁሉ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ንጉሥ አሳ ከዚያ የተገኘውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ ወስዶ ምጽጳንና በብንያም ግዛት ውስጥ የምትገኘውን የጌባዕን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራበት።
በይሁዳ ከተሞችና በመላ ሀገሪቱ ከገባዕ እስከ ቤርሳቤህ የነበሩትን ካህናት ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣ፤ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን መሠዊያዎች ሁሉ ርኩስ መሆናቸውን ዐወጀ፤ እንዲሁም የከተማይቱ ገዢ ኢያሱ ወደ ከተማይቱ ሲገቡ ከዋናው ቅጽር በር በስተ ግራ በኩል ባሠራው ቅጽር በር አጠገብ የሚገኙትን መስገጃዎች አፈራረሰ።
ዮናታን ጌባዕ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጣለ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ይህን ወሬ ሰሙ፤ ሳኦልም መልእክተኞችን ልኮ በሀገሩ ሁሉ እምቢልታ በማስነፋት ዕብራውያን ለጦርነት ጠራ።