La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 11:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነዚህም ሁሉ ነገሥታት ኀይላቸውን አስተባብረው እስራኤላውያንን ለመውጋት በሜሮም ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነዚህ ሁሉ ነገሥታት እስራኤልን ለመውጋት ኀይላቸውን አስተባብረው በማሮን ውሃ አጠገብ በአንድነት ሰፈሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነዚህም ነገሥታት ሁሉ ኃይላቸውን አስተባብረው እስራኤልን ለመውጋት መጡ፤ በማሮንም ውኃ አጠገብ በአንድ ላይ ሰፈሩ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ዚ​ህም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በማ​ሮን ውኃ አጠ​ገብ አንድ ሆነው ተያ​ያ​ዙ​አ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነዚህም ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበው እስራኤልን ለመውጋት መጥተው በማሮን ውኃ አጠገብ አንድ ሆነው ሰፈሩ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 11:5
9 Referencias Cruzadas  

ሶርያውያን በእስራኤላውያን ድል እንደ ተመቱ በተገነዘቡ ጊዜ ሠራዊታቸውን ሁሉ በአንድነት አሰባሰቡ፤


እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶቼ እንዴት ብዙዎች ናቸው! ብዙዎችም በጠላትነት በእኔ ላይ ተነሥተዋል፤


ነገር ግን ባዩአት ጊዜ ደነገጡ፤ ፈርተውም ሸሹ።


እናንተ አሕዛብ ጦርነትን ዐወጁ! ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ፤ እናንተም የሩቅ አገር ሰዎች ሁሉ አድምጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ! ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ፤ አሁንም ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ።


እነርሱም ከነወታደሮቻቸው ስለ መጡ፥ የሠራዊቱ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ ሆነ፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ነበራቸው።


እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራ፤ ስለ እስራኤል በመዋጋት ነገ ይህን ጊዜ ሁሉንም እንደ ሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ አንተም የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው።


ኀይላቸውን በአንድነት አስተባብረው በኢያሱና በእስራኤላውያን ላይ ለመዝመት መጡ።


እነርሱ ተአምራት የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ እነዚህ መናፍስት ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት ሰዎችን ለመሰብሰብ ወደ ዓለም ነገሥታት ሁሉ ይሄዳሉ።