አስቀድሞ በነገራቸው መሠረት ዮናስ ከእግዚአብሔር ፊት የኰበለለ መሆኑን ዐወቁ፤ ስለዚህም በጣም ፈርተው “ይህን ያደረግኸው ለምንድን ነው?” አሉት።
ዮናስ 1:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባሕሩም ማዕበል እየበረታ በመሄዱ መርከበኞቹ “ይህ ማዕበል ጸጥ እንዲል በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” ሲሉ ጠየቁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባሕሩም ማዕበል እጅግ እየበረታ ስለ ሄደ፣ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አሉት፦ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን ምን እናድርግብህ?” ባሕሩ መናወጡን ቀጥሎ ነበርና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሕሩ ይታወክ ነበርና፥ ታላቅ ማዕበልም ተነሥቶ ነበርና፥ “ባሕሩ ጸጥ ይልልን ዘንድ እንግዲህ ምን እናድርግህ?” አሉት። |
አስቀድሞ በነገራቸው መሠረት ዮናስ ከእግዚአብሔር ፊት የኰበለለ መሆኑን ዐወቁ፤ ስለዚህም በጣም ፈርተው “ይህን ያደረግኸው ለምንድን ነው?” አሉት።
ዮናስም “ይህ ማዕበል በእናንተ ላይ የመጣው በእኔ በደል ምክንያት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ እኔን አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፤ ማዕበሉም ጸጥ ይልላችኋል” አላቸው።