እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።
ዮሐንስ 9:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓለም ላይ ሳለሁ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓለም እስካለሁ ድረስ የዓለም ብርሃን ነኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዓለም ሳለሁ፤ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን ነኝ።” |
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።
ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’
እነርሱም የተናገሩት ‘መሲሕ መከራ ይቀበላል፤ ከሞት በመነሣትም የመጀመሪያ ሆኖ የመዳንን ብርሃን ለእስራኤል ሕዝብና ለአሕዛብ ይገልጣል’ ብለው ነው።”