ሰዎቹም “በሕግ ተጽፎ የምናገኘው ‘መሲሕ ለዘለዓለም ይኖራል’ የሚል ነው፤ ታዲያ፥ አንተ፥ ‘የሰው ልጅ ወደ ላይ ከፍ ማለት አለበት’ እንዴት ትላለህ? ይህስ የሰው ልጅ ማን ነው?” አሉት።
ዮሐንስ 7:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ትፈልጉኛላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ነው?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበትም ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ይሆን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤’ የሚለውስ ይህ አባባል ምን ማለት ነው?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘ትሹኛላችሁ፤ አታገኙኝምም፤ እኔ ወደምሄድበት እናንተ መምጣት አትችሉም’ የሚለን ይህ ነገር ምንድን ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ፦ “ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም የሚለው ይህ ቃል ምንድር ነው?” ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ። |
ሰዎቹም “በሕግ ተጽፎ የምናገኘው ‘መሲሕ ለዘለዓለም ይኖራል’ የሚል ነው፤ ታዲያ፥ አንተ፥ ‘የሰው ልጅ ወደ ላይ ከፍ ማለት አለበት’ እንዴት ትላለህ? ይህስ የሰው ልጅ ማን ነው?” አሉት።
ልጆቼ ሆይ፥ ከእናንተ ጋር ብዙ ጊዜ አልቆይም፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁድ ባለሥልጣኖች ‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም’ እንዳልኳቸው፥ አሁንም ለእናንተ እንዲሁ እላችኋለሁ።
እንደገናም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ እሄዳለሁ፤ እናንተም እኔን ትፈልጉኛላችሁ፤ ነገር ግን ከነኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ እንጂ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም።”
የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለው ሥጋዊ ሰው ግን ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚሰጠውን ስጦታ መቀበል አይችልም፤ የስጦታው ታላቅነት የሚመረመረው በእግዚአብሔር መንፈስ አማካይነት ስለ ሆነ ሊያስተውለው አይችልም፤ እንዲያውም ይህ ለእርሱ ሞኝነት መስሎ ይታየዋል።