La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 6:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በጀልባ ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም አመሩ፤ በዚያን ሰዓት ጊዜው ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በጀልባውም ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም ለመሻገር ተነሡ። ጊዜው መሽቶ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ እነርሱ ገና አልመጣም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በታንኳም ገብተው በባሕር ማዶ ወደ ቅፍርናሆም ይመጡ ነበር። ከወዲሁ ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ታን​ኳም ወጡ፤ ወደ ባሕር ማዶ ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆ​ምም ሄዱ፤ እነ​ሆም፥ ፈጽሞ ጨለማ ሆነ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ እነ​ርሱ ገና አል​መ​ጣም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በታንኳም ገብተው በባሕር ማዶ ወደ ቅፍርናሆም ይመጡ ነበር። አሁንም ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፤

Ver Capítulo



ዮሐንስ 6:17
6 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስ ወዲያውኑ ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ሆነው ወደ ማዶ ወደ ቤተ ሳይዳ ተሻግረው እንዲቀድሙት አዘዛቸው።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከእናቱና ከወንድሞቹ፥ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በዚያም ጥቂት ቀኖች ተቀመጡ።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ውሃውን የወይን ጠጅ ወደ ለወጠባት በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ወደ ቃና ከተማ እንደገና ተመለሰ፤ በዚያን ጊዜ በቅፍርናሆም ልጁ የታመመበት አንድ የቤተ መንግሥት ሹም ነበረ።


ኀይለኛ ነፋስ ይነፍስ ስለ ነበር፤ ባሕሩ ተናወጠ።


ኢየሱስ ይህን የተናገረው በቅፍርናሆም በምኲራብ በሚያስተምርበት ጊዜ ነበር።