ዮሐንስ 5:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ የላከውን ስለማታምኑ የእርሱ ቃል በእናንተ ዘንድ አይኖርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የላከውንም ስላላመናችሁ ቃሉ በእናንተ አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ የላከውንም እናንተ አታምኑምና፤ በእናንተ ዘንድ የሚኖር ቃሉ የላችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃሉም የላችሁም፤ በእናንተ ዘንድም አይኖርም፤ እርሱ የላከውን አላመናችሁምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም የላከውን እናንተ አታምኑምና በእናንተ ዘንድ የሚኖር ቃሉ የላችሁም። |
ክፉ ሰዎች ቸርነት ብታደርግላቸው እንኳ መልካም መሥራትን አይማሩም፤ በዚህ ጽድቅ በሰፈነበት ምድር እያሉ እንኳ ክፋት ከማድረግ አይቈጠቡም፤ ታላቅነትህንም አይገነዘቡም።
በሕዝቦች ዘንድ በጣም ለተናቅህና ለተጠላህ፥ ለገዢዎችም አገልጋይ ለሆንክ ለአንተ፥ አዳኙ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ነገሥታት ሲያዩህ ይነሡልሃል፤ ልዑላንም ይሰግዱልሃል፤ ይህም የሚሆነው በመረጠህ በታማኙ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ምክንያት ነው።”
የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።
ይህን የሕግ መጽሐፍ ምን ጊዜም ከማንበብ አትቈጠብ፤ በእርሱ የተጻፈውን ሁሉ መፈጸም ትችል ዘንድ እርሱን ሌሊትና ቀን አሰላስለው፤ ይህንን ብታደርግ፥ ሁሉ ነገር በተቃና ሁኔታ ይሳካልሃል።
ልጆች ሆይ፥ አብን ስላወቃችሁት ጽፌላችኋለሁ። አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያው የነበረውን ስላወቃችሁት ጽፌላችኃለሁ። ወጣቶች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁና የእግዚአብሔር ቃል በልባችሁ ስለሚኖር፥ ሰይጣንንም ስላሸነፋችሁ ጽፌላችኋለሁ።