እርሱ ራሱ “ነቢይ በገዛ አገሩ አይከበርም” ብሎ ተናግሮ ነበር።
ነቢይ በገዛ አገሩ እንደማይከበር ኢየሱስ ራሱ ተናግሮ ነበርና።
ነቢይ በገዛ አገሩ እንዳይከበር ኢየሱስ ራሱ መስክሮአልና።
ነቢይ በገዛ ሀገሩ እንደማይከብር እርሱ ራሱ ጌታችን ኢየሱስ መሰከረ።
በዚህም ምክንያት ተሰናክለውበት ሳይቀበሉት ቀሩ። ኢየሱስ ግን፦ “ነቢይ የማይከበረው በሀገሩና በገዛ ቤቱ ብቻ ነው” አላቸው።
ኢየሱስ ግን፥ “ነቢይ በሌሎች ዘንድ ይከበራል፤ በገዛ አገሩ፥ በዘመዶቹና በቤተ ሰቡ መካከል ግን ይናቃል፤” ሲል መለሰላቸው።
በእውነት እላችኋለሁ፤ ነቢይ በገዛ አገሩ ሰዎች ዘንድ አይከበርም።