La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 21:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስም “ልጆች ሆይ! አንዳች ዓሣ አላችሁን?” አላቸው። እነርሱም “ምንም የለንም” አሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም፣ “ልጆች፣ ዓሣ አላችሁ?” አላቸው። እነርሱም፣ “የለንም” አሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስም “ልጆች ሆይ! አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁን?” አላቸው። “የለንም” ብለው መለሱለት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ልጆች ሆይ አን​ዳች የሚ​በላ ነገር አላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የለም” አሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም፦ “ልጆች ሆይ፥ አንዳች የሚበላ አላችሁን?” አላቸው። “የለንም” ብለው መለሱለት።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 21:5
10 Referencias Cruzadas  

ኤልያስም ተነሥቶ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ በድንጋይ ሙቀት የበሰለ የዳቦ ሙልሙልና አንድ ገንቦ ውሃ በራስጌው ተቀምጦ አየ፤ ከበላና ከጠጣም በኋላ ተመልሶ ተኛ፤


በእግዚአብሔር ታምነህ መልካምን አድርግ፤ በምድሪቱም በሰላም ትኖራለህ።


በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፥ “ይህ ቦታ ምድረ በዳ ነው፤ ቀኑም መሽቶአል፤ ስለዚህ ሕዝቡ በአቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች ሄደው ምግባቸውን እንዲገዙ አሰናብታቸው” አሉት።


ጥቂት ትናንሽ ዓሣዎችም ነበሩአቸው፤ ስለ ዓሣዎቹም እግዚአብሔርን ካመሰገነ በኋላ ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ደቀ መዛሙርቱን አዘዘ።


ስለዚህም አምላኬ ከክብሩ ብልጽግና በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል።


ከገንዘብ ፍቅር ራቁ፤ ያላችሁ ይብቃችሁ፤ እግዚአብሔር “ከቶ አልጥልህም፤ ፈጽሞም አልተውህም” ብሎአል።


አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን ስላወቃችሁት እጽፍላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ፥ ሰይጣንን ስላሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።


ልጆቼ ሆይ! ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ “የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣል” ሲባል ሰምታችኋል፤ እነሆ፥ አሁን እንኳ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ በዚህ ምክንያት የመጨረሻው ሰዓት መሆኑን እናውቃለን።