ዮሐንስ 20:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከሞት መነሣት ይገባዋል” የሚለውን የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ገና አልተገነዘቡም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም ኢየሱስ ከሙታን መነሣት እንዳለበት ገና ከመጽሐፍ ስላልተረዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከሙታን መነሣት ይገባዋል” የሚለውን የመጽሐፉን ቃል ገና አላወቁም ነበርና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሙታን ተለይቶ ይነሣ ዘንድ እንደ አለው በመጻሕፍት የተጻፈውን ገና አላወቁም ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሙታን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው የሚለውን የመጽሐፉን ቃል ገና አላወቁም ነበርና። |
ልዑል እግዚአብሔር የሞትን ኀይል ለዘለዓለም ያጠፋል! ከሰዎችም ሁሉ ዐይን እንባን ያብሳል፤ ወገኖቹ በዓለም ሁሉ ላይ የተቀበሉትን ኀፍረት ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ራሱ ይህን ተናግሮአል።
ሙታንህ ተነሥተው ሕያዋን ይሆናሉ፤ እናንተ በመቃብር ውስጥ የምትኖሩ፥ ተነሥታችሁ የደስታ መዝሙር ዘምሩ! አንጸባራቂው ጠል ምድርን እንደሚያድስ እግዚአብሔርም ከሞቱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን ተነሥተው በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል።
ከሲኦል ኀይል እታደጋቸዋለሁን? ከሞትስ አድናቸዋለሁን? ሞት ሆይ! መቅሠፍቶችህ የት አሉ? ሲኦል ሆይ! አጥፊነትህ የት አለ? እኔኮ አልራራላቸውም፤
ስለዚህ ኢየሱስ ከሞት በተነሣ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ይህን ተናግሮ እንደ ነበረ አስታወሱ፤ በዚህ ምክንያት በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈውንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።