ዮሐንስ 16:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንግዲህ ይህ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ’ የሚለው ነገር ምንድን ነው? የሚናገረውን ነገር አናውቅም” በመባባል መላልሰው ተጠያየቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ጥቂት ጊዜ’ ማለቱስ ምን ይሆን? የሚለውም ነገር አልገባንም” እያሉ ይጠያየቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንግዲህ ‘ጥቂት’ ሲል ምን ማለቱ ነው? የሚናገረውን አናውቅም” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይህ ጥቂት የሚለን ምንድነው? የሚናገረውን አናውቅም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “እንግዲህ፦ “ጥቂት” የሚለው ይህ ምንድር ነው? የሚናገረውን አናውቅም” አሉ። |
ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶች፥ “ይህ፥ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ደግሞ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ፤ ደግሞ ወደ አብ እሄዳለሁ’ የሚለን ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ።
ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደ ፈለጉ ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሳችሁ የምትጠያየቁ፥ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ደግሞም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ’ ስላልኳችሁ ነውን?
እስከ አሁን በነበረው ጊዜ እናንተ አስተማሪዎች መሆን በተገባችሁ ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል የመጀመሪያውን ትምህርት ሌላ ሰው እንደገና እንዲያስተምራችሁ ያስፈልጋል፤ በዚህ ዐይነት የሚያስፈልጋችሁ ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።