ዮሐንስ 16:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ፥ ይህን ሁሉ የነገርኳችሁ እምነታችሁ እንዳይናወጥ ብዬ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን ሁሉ የነገርኋችሁ እንዳትሰናከሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንዳትሰናከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንዳትሰናከሉ ይህን ነገርኋችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። |
ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በልቡ ውስጥ ሥር አልሰደደም፤ ስለዚህ በቃሉ ምክንያት አንዳች ችግር ወይም ስደት በደረሰበት ጊዜ ቶሎ ይሰናከላል።
ይህንን ለእናንተ መናገሬ ግን ጊዜው ሲደርስ ምን እንዳልኳችሁ እንድታስታውሱ ነው።” “ይህን ሁሉ ከአሁን በፊት ያልነገርኳችሁ ከእናንተ ጋር ስለ ነበርኩ ነው፤
ስለዚህ ወንድምህን ላለማሰናከል ሥጋን አለመብላት፥ የወይን ጠጅን አለመጠጣት፥ ወይም ማንኛውንም የሚያሰናክል ነገር አለማድረግ መልካም ነው።
ደግሞም፥ “እነሆ! ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ፤ እነሆ! ሰዎችን አደናቅፎ የሚጥል አለት” ይላል። እነርሱ ቃሉን ባለማመናቸው ይሰናከላሉ፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።