ዮሐንስ 12:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ድምፅ የመጣው ለእናንተ ሲል ነው እንጂ ለእኔ ሲል አይደለም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ “ይህ ድምፅ የመጣው ስለ እኔ ሳይሆን ስለ እናንተ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ “ይህ ድምፅ ስለ እናንተ መጥቷል እጂ ስለ እኔ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ይህ ቃል የመጣ ስለ እናንተ ነው እንጂ ስለ እኔ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ “ይህ ድምፅ ስለ እናንተ መጥቶአል እጂ ስለ እኔ አይደለም። |
እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁ፤ እርሱ ምንም እንኳ ሀብታም ቢሆን በእርሱ ድኻ መሆን እናንተ ሀብታሞች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ብሎ ድኻ ሆነ።