ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱ ግን “ለልጄ እያለቀስሁ ወደ ሙታን ዓለም እወርዳለሁ” በማለት መጽናናትን እምቢ አለ። ስለዚህ ስለ ልጁ ማዘኑን ቀጠለ።
ዮሐንስ 11:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአይሁድም ብዙዎች ማርታንና ማርያምን ስለ ወንድማቸው ሞት ለማጽናናት ወደ እነርሱ መጥተው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙዎች አይሁድም ማርታንና ማርያምን ስለ ወንድማቸው ሞት ሊያጽናኗቸው መጥተው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአይሁድም ብዙዎች ስለ ወንድማቸው ሊያጽናኑአቸው ወደ ማርታና ወደ ማርያም መጥተው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአይሁድም ስለ ወንድማቸው ሊያጽናኑአቸው ወደ ማርያምና ወደ ማርታ የሄዱ ብዙዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአይሁድም ብዙዎች ስለ ወንድማቸው ሊያጽናኑአቸው ወደ ማርታና ወደ ማርያም መጥተው ነበር። |
ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱ ግን “ለልጄ እያለቀስሁ ወደ ሙታን ዓለም እወርዳለሁ” በማለት መጽናናትን እምቢ አለ። ስለዚህ ስለ ልጁ ማዘኑን ቀጠለ።
ንጉሥ ዳዊትም “አባቱ ናዖስ ለእኔ እንዳደረገልኝ ሁሉ እኔም ለልጁ ለሐኑን ታማኝ ወዳጅ በመሆን ወሮታውን እከፍላለሁ” አለ። ስለዚህም ዳዊት የሐዘን ተካፋይነቱን ለመግለጥ መልእክተኞች ላከ። መልእክተኞቹም ዐሞን በደረሱ ጊዜ፥
ኀያላን የሆኑ ሰዎች ሄደው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ በመውሰድ ወደ ያቤሽ አመጡ፤ በዚያም በወርካ ዛፍ ሥር ከቀበሩአቸው በኋላ ሰባት ቀን በሙሉ ጾሙ።
የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ፥ የሹሐ አገር ሰው የሆነው ቢልዳድና የናዕማ አገር ሰው የሆነው ጾፋር፥ እነዚህ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ነበሩ። እነርሱም በኢዮብ ላይ የደረሰውን ሥቃይ በሰሙ ጊዜ ሐዘናቸውን ሊገልጹለትና ሊያጽናኑት ከየአገራቸው ተጠራርተው በአንድነት ወደ ኢዮብ መጡ።
በዚህ ጊዜ የኢዮብ ወንድሞች፥ እኅቶችና ቀድሞ የሚያውቁት ሰዎች ሁሉ ሊጐበኙት መጡ፤ በቤቱም ከእርሱ ጋር ተመገቡ፥ ሐዘናቸውን በመግለጥ እግዚአብሔር ስላደረሰበት ብርቱ መከራ አጽናኑት፤ እያንዳንዳቸውም የብርና የወርቅ ቀለበት ስጦታ አደረጉለት።
በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጒንጮችዋ ላይ ይወርዳል፤ ከአፍቃሪዎችዋ ሁሉ እርስዋን የሚያጽናና አንድ እንኳ የለም፤ ወዳጆችዋ የነበሩ ሁሉ ከድተዋታል፤ በጠላትነትም ተነሥተውባታል።
“ጠላቶቼ ሁሉ ማንም የሚያጽናናኝ ሰው በሌለበት እንዴት እንደምቃትትና እንደምቸገር ሰሙ፤ አንተ ያደረግኸው መሆኑንም ዐውቀው ተደሰቱ፤ በእነርሱ ላይ ልታመጣባቸው የወሰንከውን ቀን አምጣና እንደ እኔ ይሁኑ።
አደፍዋ በቀሚስዋ ላይ ይታያል፤ ለወደፊት ምን እንደሚደርስባት አላሰበችም፤ አወዳደቅዋ የሚያሰቅቅ ነው፤ የሚያጽናናት ከቶ የለም፤ ጠላቶችዋ ድል ስላደረግዋት፥ መከራዋን እንዲመለከትላት ወደ እግዚአብሔር ጸለየች።
ምን ልበላችሁ? ከምንስ ጋር ላነጻጽራችሁ? የተወደደችው ከተማ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! እንዳጽናናችሁ ከምን ጋር ላመሳስላችሁ? በተለይ የኢየሩሳሌም ከተማ ሕዝብ ሆይ! የሚደርስባችሁ ጥፋት እንደ ባሕር መጠኑ ሰፊ ስለ ሆነ፥ ማን ሊፈውሳችሁ ይችላል?
የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ወደ ዮሐንስ ልከው፦ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ባስጠየቁት ጊዜ የሰጠው ምስክርነት የሚከተለው ነው፤
እርስዋን ለማጽናናት መጥተው በቤት ውስጥ አብረዋት የነበሩ አይሁድ ማርያም በፍጥነት ተነሥታ ስትወጣ አይተው ወደ አልዓዛር መቃብር ሄዳ የምታለቅስ መስሎአቸው ተከተሉአት።
ደቀ መዛሙርቱም “መምህር ሆይ! አይሁድ ከጥቂት ጊዜ በፊት ሊወግሩህ ይፈልጉ ነበር፤ ታዲያ እንደገና ወደዚያ ተመልሰህ ትሄዳለህን?” አሉት።