ዳዊትም ሕዝቡን ይቀሥፍ የነበረውን መልአክ አይቶ እግዚአብሔርን “በደል የፈጸምኩት እኔ ነኝ፤ እኔም ራሴ ክፉ ነገርን አደረግሁ፤ ታዲያ ይህ ምስኪን ሕዝብ ምን በደለህ? ይህ መቅሠፍት በእርሱ ላይ ከሚወርድ ይልቅ በእኔና በቤተሰቤ ላይ ይሁን” ሲል ጠየቀ።
ዮሐንስ 10:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍሱን ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። |
ዳዊትም ሕዝቡን ይቀሥፍ የነበረውን መልአክ አይቶ እግዚአብሔርን “በደል የፈጸምኩት እኔ ነኝ፤ እኔም ራሴ ክፉ ነገርን አደረግሁ፤ ታዲያ ይህ ምስኪን ሕዝብ ምን በደለህ? ይህ መቅሠፍት በእርሱ ላይ ከሚወርድ ይልቅ በእኔና በቤተሰቤ ላይ ይሁን” ሲል ጠየቀ።
የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥ ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ።
እንደ እረኛ ለመንጋው እንክብካቤ ያደርጋል፤ ግልገሎቹን በአንድነት ይሰበስባል፤ በእጆቹም ዐቅፎ ይወስዳቸዋል፤ እናቶቻቸውንም በርኅራኄ ይመራቸዋል።
ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
“የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ጠባቂዎች ላይ ትንቢት ተናገርባቸው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን ሁሉ በትንቢት እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘መንጋውን መንከባከብና መጠበቅ ትታችሁ ራሳችሁን የምትጠብቁ እናንተ የእስራኤል እረኞች ወዮላችሁ!
እርሱ በእግዚአብሔር ኀይል ተነሥቶ የበግ መንጋውን ያሰማራል፤ ይህንንም የሚያደርገው በግርማዊው በእግዚአብሔር በአምላኩ ስም ነው፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ስለሚሆን እነርሱ ያለ ስጋት ይኖራሉ።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ።
ክርስቶስ እንደ ወደደንና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ሕይወቱን ስለ እኛ አሳልፎ እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ኑሩ።
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
ፍቅር ምን እንደ ሆነ የምናውቀው ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወቱን ለእኛ አሳልፎ ስለ ሰጠን ነው፤ እኛም ሕይወታችንን ስለ ወንድሞቻችን አሳልፈን መስጠት ይገባናል።