ስለዚህም ተመልሰው መጥተው በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በምሰጣቸውም የእህል፥ የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይት፥ የበግና የቀንድ ከብት በረከት ሁሉ ተድላ ደስታ ያደርጋሉ፤ በቂ ውሃ እንዳገኘች የተክል ቦታ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህ ወዲያም አያዝኑም።
ኢዩኤል 2:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ እህል፥ የወይን ጠጅና የወይራ ዘይት እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አሕዛብ መዘባበቻ እንዲያደርጉአችሁ አልፈቅድም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል፤ “እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት፣ እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ የሕዝቦች መዘባበቻ አላደርጋችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም መልሶ ሕዝቡን፦ እነሆ፥ እህልንና ወይንን ዘይትንም እልክላችኋለሁ፤ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም መልሶ ሕዝቡን፥ “እነሆ እህልንና ወይንን፥ ዘይትንም እሰድድላችኋለሁ፤ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም መልሶ ሕዝቡን፦ እነሆ፥ እህልንና ወይንን ዘይትንም እሰድድላችኋለሁ፥ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም። |
ስለዚህም ተመልሰው መጥተው በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በምሰጣቸውም የእህል፥ የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይት፥ የበግና የቀንድ ከብት በረከት ሁሉ ተድላ ደስታ ያደርጋሉ፤ በቂ ውሃ እንዳገኘች የተክል ቦታ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህ ወዲያም አያዝኑም።
ምድሪቱ ከእንግዲህ ወዲህ የሕዝቦች ማላገጫ አትሆንም፤ በንቀትም አይመለከቱአትም፤ ምድሪቱንም ዳግመኛ ልጅ አልባ የሚያደርጋት አይኖርም። እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
የቀድሞውን የወይን ተክል እመልስላታለሁ፤ የመከራንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ፤ እዚያም ከግብጽ ስትወጣ በወጣትነትዋ ወራት በነበራት ሁኔታ በደስታ ትዘምራለች።
ሰብላችሁም እጅግ የበዛ ከመሆኑ የተነሣ ገና መከር መሰብሰብ ሳትጨርሱ፥ የወይን ዘለላ የምትቈርጡበት ጊዜ ይደርሳል፤ የወይን ዘለላም ቈርጣችሁ ሳትጨርሱ እህል የምትዘሩበት ወቅት ይደርሳል፤ ለምግብ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ታገኛላችሁ፤ በምድራችሁም በሰላም ትኖራላችሁ።
እህላቸውን በሰላም ዘርተው ፍሬውን ይሰበስባሉ የወይን ተክሎቻቸውም ያፈራሉ። በቂ ዝናብ ስለሚዘንብ ምድሪቱ ብዙ ሰብል ትሰጣለች፤ ከስደት ለተረፉት ሕዝብ ይህን ሁሉ በረከት እሰጣለሁ።
ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር የክረምቱንና የበልጉን ዝናብ በወቅቱ ለምድራችሁ ይልካል፤ በዚህም ዐይነት ለእናንተ ሲሳይ የሚሆነው እህል፥ ወይን ጠጅና የወይራ ዘይት፥
ናዖሚ በሞአብ አገር ሳለች፥ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ምሕረት እንዳደረገላቸውና ብዙ መከር እንደ ሰጣቸው ሰማች፤ ስለዚህ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከሞአብ ወደ እስራኤል ለመመለስ ተነሣች።