“እኛ ግን አሁንም እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ከእርሱም ፈቀቅ አላልንም፤ የአሮን ልጆች የሆኑ ካህናትም እግዚአብሔርን ማገልገላቸውን አላቋረጡም፤ ሌዋውያንም እንደ ወትሮው ሁሉ ካህናትን ይረዳሉ፤
ኢዩኤል 1:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ቤት መባ ሆኖ የሚቀርብ እህልም ሆነ የወይን ጠጅ በመታጣቱ፥ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሆኑት ካህናት ያለቅሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን፣ ከእግዚአብሔር ቤት ተቋርጧል፤ በእግዚአብሔርም ፊት የሚያገለግሉ፣ ካህናት ያለቅሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከጌታ ቤት ተወግዶአል፥ የጌታ አገልጋዮች ካህናቱ አለቀሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሥዋዕቱና የመጠጡ ቍርባን ከእግዚአብሔር ቤት ተወግዶአል፤ በእግዚአብሔርም መሠውያ የምታገለግሉ ካህናቱ፥ አልቅሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእህሉ ቍርባንና የመጠጡ ቍርባን ከእግዚአብሔር ቤት ተወግዶአል፥ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ካህናቱ አለቀሱ። |
“እኛ ግን አሁንም እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ከእርሱም ፈቀቅ አላልንም፤ የአሮን ልጆች የሆኑ ካህናትም እግዚአብሔርን ማገልገላቸውን አላቋረጡም፤ ሌዋውያንም እንደ ወትሮው ሁሉ ካህናትን ይረዳሉ፤
“ወንድምህን አሮንንና ልጆቹን ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን ወደ አንተ አቅርብ፤ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝም ዘንድ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ለያቸው።
እናንተ ግን “የእግዚአብሔር ካህናትና የአምላካችን አገልጋዮች” ተብላችሁ ትጠራላችሁ። በሕዝቦች ሀብት ትደሰታላችሁ፤ በብልጽግናቸውም ትከብራላችሁ።
ማንም ሰው በዓላቱን ለማክበር ስለማይመጣ የጽዮን መንገዶች ጭር ይላሉ፤ በሮችዋ ሁሉ ባዶ ናቸው፤ ካህናትዋ ይቃትታሉ ልጃገረዶችዋ በሐዘን ይጨነቃሉ የጽዮንም ዕድል ፈንታ የመረረ ይሆናል።
በዚያም ለእግዚአብሔር የወይን ጠጅ መባ ማቅረብ አይችሉም፤ መሥዋዕታቸውም እግዚአብሔርን አያስደስትም፤ የእነርሱ እንጀራ ሲርባቸው የሚበሉት እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ አይደለም፤ ስለዚህ ለእነርሱ የእዝን እንጀራ ይሆናል፤ እርሱንም የሚመገብ ሁሉ ይረክሳል።
ለአምላካችሁ የምታቀርቡት የእህልም ሆነ የወይን ጠጅ መባ ስለሌለ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች የሆናችሁ ካህናት! ኑና ማቅ ለብሳችሁ ሌሊቱን ሁሉ አልቅሱ! እናንተም በመሠዊያው ላይ የምታገለግሉ ዋይ! ዋይ! በሉ።
ምናልባት እግዚአብሔር አምላካችሁ ቊጣውን መልሶ፥ በረከቱን ይሰጣችሁ ይሆናል፤ እናንተም በዚያን ጊዜ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቊርባን ታቀርባላችሁ።
እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናት፥ በመሠዊያውና በመተላለፊያው መካከል ሆነው ያልቅሱ፤ “ጌታ ሆይ! ለሕዝብህ ራራ፤ አሕዛብ አምላካችሁ የት አለ? በማለት እንዲንቁንና እንዲዘባበቱብን አታድርግ” ይበሉ።