ኢዩኤል 1:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለባቱኤል ልጅ ለኢዩኤል ከእግዚአብሔር የመጣለት የትንቢት ቃል ይህ ነው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ባቱኤል ልጅ ወደ ኢዩኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ባቱኤል ልጅ ወደ ኢዩኤል የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ባቱኤል ልጅ ወደ ኢዮኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ባቱኤል ልጅ ወደ ኢዩኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። |
በከለዳውያን ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የእግዚአብሔር ቃል የቡዚ ልጅ ወደ ሆንኩት ወደ ካህኑ ወደ እኔ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ የእግዚአብሔርም ኀይል በእኔ ላይ ነበረ።
ዖዝያን፥ ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ በይሁዳ ተከታትለው በነገሡባቸው ዘመናት፤ እንዲሁም የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረበት ዘመን፥ እግዚአብሔር ለብኤር ልጅ ለሆሴዕ የገለጠለት የትንቢት ቃል ይህ ነው።