ኢዮብ 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን ችግር ስለ መጣብህ ተስፋ ቢስ ሆነሃል፤ ችግሩም ስለ በረታብህ ተስፋ ቈርጠሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ግን መከራ አገኘህ፣ አንተም ተስፋ ቈረጥህ፤ ሸነቈጠህ፤ ደነገጥህም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን ግን በአንተ ላይ መጥቷል፥ አንተም ደከምህ፥ ደርሶብሃል፥ አንተም ተረበሽህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን ግን ሕማም በአንተ ላይ መጥቶ ዳሰሰህ። አንተም ተቸገርህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን ግን በአንተ ላይ መጥቶአል፥ አንተም ደከምህ፥ ደርሶብሃል፥ አንተም ተቸገርህ። |
እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ አድርጎ እንዲህ ሲል የመከራችሁን ረስታችኋል፤ “ልጄ ሆይ! የጌታን ተግሣጽ አታቃል፤ በቀጣህም ጊዜ ተስፋ አትቊረጥ፤