Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 6:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “ለወዳጁ ያለውን ታማኝነት የሚነሣ ሰው እግዚአብሔርን መፍራቱን የተወ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ለወዳጁ በጎነት የማያሳይ ሰው፣ ሁሉን ቻዩን አምላክ መፍራት ትቷል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “ቸርነትን ለወዳጁ የሚነፍግ፥ ሁሉን ቻይ አምላክን መፍራት የተወ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ምሕ​ረቱ ቸል አለኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ጐ​በ​ኘ​ኝም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ተ​ኝም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሁሉን የሚችለውን የአምላክን መፍራት ለሚተው፥ ለመዛል ለቀረበው ስንኳ ወዳጁ ቸርነትን ሊያሳይ ይገባል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 6:14
16 Referencias Cruzadas  

አብርሃምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘እዚህ ቦታ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የለም’ ብዬ በማሰብ ‘ሚስቴን ለመውሰድ በመፈለግ ይገድሉኛል’ ብዬ ስለ ሰጋሁ ነው፤


የግብዣዎቹ ቀኖች ከተፈጸሙ በኋላ ኢዮብ በማለዳ ተነሥቶ ልጆቹን ያስጠራና በእያንዳንዱ ልጁ ስም መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፤ ይህንንም የሚያደርገው “ምናልባት ከልጆቼ አንዱ እግዚአብሔርን በመስደብ በድሎ ይሆናል!” በሚል ስጋት ልጆቹን ከኃጢአት ለማንጻት ነበር። ኢዮብ ይህን ሥርዓት ሳያቋርጥ ዘወትር ይፈጽም ነበር።


አንተ እግዚአብሔርን መፍራት ትተሃል፤ ለእግዚአብሔር የሚገባውንም አምልኮ ታደናቅፋለህ።


እንዲሁም በአንደበቴ ባበረታታኋችሁና እናንተንም ለማጽናናት ብዙ መናገር በቻልኩ ነበር።


“ወዳጆቼ ሆይ! የእግዚአብሔር እጅ ስለ መታኝ እባካችሁ እናንተ እዘኑልኝ! ራሩልኝም!


ወዳጅ ምን ጊዜም ቢሆን ወዳጁን ይወዳል፤ ወንድም የሚወለደው የወንድሙን ችግር ለመካፈል ነው።


በመከራ ጊዜ በማይታመን ሰው ላይ መደገፍ በተነቃነቀ ጥርስ እንደማኘክና በተሰበረ እግር እንደ መራመድ ያኽል ነው።


“እኔ የሠራዊት አምላክ ለሕዝቤ የሰጠሁት ትእዛዝ ይህ ነበር፤ ‘በትክክል ፍረዱ፥ እርስ በርሳችሁም አንዳችሁ ለሌላው ምሕረትና ርኅራኄን አድርጉ፤


ሌላው ወንጀለኛ ግን እንዲህ ብሎ ገሠጸው፦ “አንተ በተመሳሳይ ፍርድ ላይ እያለህ እግዚአብሔርን አትፈራምን?


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።


አንዱ የአካል ክፍል ሲሠቃይ ሌሎችም የአካል ክፍሎች በሙሉ አብረው ይሠቃያሉ፤ አንዱ የሰውነት ክፍል ሲከበር ሌሎቹም የሰውነት ክፍሎች አብረው ከእርሱ ጋር ይደሰታሉ።


አንድ ሰው ሲደክም እኔ አብሬው ያልደከምኩት መቼ ነው? አንድ ሰው በኃጢአት ሲሰናከል እኔም ያልተናደድኩት መቼ ነው?


ከእናንተ እያንዳንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህ ዐይነት የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።


ከእነርሱ ጋር አብራችሁ እንደ ታሰራችሁ ያኽል ሆናችሁ እስረኞችን አስታውሱ፤ እናንተም እንደ እነርሱ መከራ የምትቀበሉ ያኽል ሆናችሁ መከራ የሚቀበሉትን አስቡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios