በዚያን ጊዜ ምድር ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍ ነበር።
ኢዮብ 38:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሕርን በደመና የጋረድኩ በድቅድቅ ጨለማም የሸፈንኩ እኔ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናውን ልብሱ፣ ጨለማንም መጠቅለያው አደረግሁለት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደመናውን ለልብሱ፥ ጨለማንም ለመጠቅለያው አደረግሁ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመናውን ልብስ አደረግሁላት። በጭጋግም ጠቀለልኋት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደመናውን ለልብሱ፥ ጨለማንም ለመጠቅለያው አደረግሁ፥ |
በዚያን ጊዜ ምድር ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍ ነበር።
ወደ ሰማይ ወጥቶ የወረደ ማን ነው? ነፋስን በእጁ የጨበጠ፥ ውሃን በልብሱ የቋጠረ፥ የምድርን ዳርቻ ያጸና ማን ነው? የሰውዬው ስም ማነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? ታውቅ እንደሆን ንገረኝ፤