ኢዮብ 3:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ ቀን ወደ ጨለማ ይለወጥ፤ የሰማይ አምላክ አያስበው፤ ብርሃን ከቶ አይታይበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፤ ብርሃንም አይብራበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያ ቀን ጨለማ ይሁን፥ እግዚአብሔር ከላይ አይፈልገው፥ ብርሃንም አይብራበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያች ቀን ጨለማ ትሁን፤ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከታት፥ ብርሃንም አይብራባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያ ቀን ጨለማ ይሁን፥ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፥ ብርሃንም አይብራበት። |
ያ ቀን የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤ የጧት ፀሐይ ወገግታ በተራሮች ላይ እንደሚያንሰራፋ፥ ታላቅና ኀያል የአንበጣ መንጋ በየቦታው ይንሰራፋል። ይህን የሚመስል ነገር ከዚህ በፊት አልታየም፤ ከእንግዲህ ወዲህም ምን ጊዜም ቢሆን አይታይም።
እናንተ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት የምትጠባበቁ ወዮላችሁ! ያ ቀን የጨለማ እንጂ የብርሃን ቀን ስላይደለ ለምን ያንን ቀን ትጠባበቃላችሁ?
አምስተኛው መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት ጨለማ ሆነ፤ ሰዎች ከሥቃያቸው የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር፤