ኢዮብ 15:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በውኑ ብልኅ ሰው እንደ ነፋስ የማይጨበጥ ነገር ይናገራልን? በሆዱስ ጐጂ የሆነ ሐሳብ ሊኖረው ይገባልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጠቢብ ሰው በከንቱ ንግግር መልስ ይሰጣልን? ወይስ በምሥራቅ ነፋስ ሆዱን ይሞላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በውኑ ጠቢብ ሰው እንደ ነፋስ በሆነ እውቀት ይመልሳልን? ሆዱንስ በምሥራቅ ነፋስ ይሞላልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በውኑ ጠቢብ ሰው እንደ ነፋስ በሆነ ዕውቀት ይመልሳልን? ሆዱንስ በሥቃይ ይሞላልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ጠቢብ ሰው እንደ ነፋስ በሆነ እውቀት ይመልሳልን? በሆዱስ የምሥራቅን ነፋስ ይሞላልን? |
“የእስራኤል ሕዝብ ነፋስን ለመጨበጥ በመሞከርና ቀኑን ሙሉ የምሥራቅ ነፋስን ሲያሳድዱ በመዋል ከንቱ ሆነዋል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛሉ፤ ከአሦር ጋር ይዋዋላሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የወይራ ዘይትን ወደ ግብጽ ይልካሉ።”
እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ የያዕቆብንም ልጆች እንደ አካሄዳቸው ይቀጣቸዋል፤ ባደረጉትም ክፉ ሥራ መጠን ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል።