ኢዮብ 10:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንተ ዐይን እንደ ሰው ዐይን ነውን? ወይስ የምታየው እንደ ሰው ነውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ዐይንህ የሥጋ ለባሽ ዐይን ነውን? ሟች የሆነ የሰው ልጅ እንደሚያይ ታያለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ የሥጋ ዐይን አለህን? ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ የሰው ዐይን አለህን? ወይስ መዋቲ ሰው እንደሚያይ ታያለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ የሥጋ ዓይን አለህን? ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለህን? |
እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ራሳችሁን በሰው ፊት ጻድቅ ታስመስላላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ፊት ክብር ያለው መስሎ የሚታይ፥ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው።”
እግዚአብሔር ግን “የኤሊአብን ቁመት መርዘምና መልከ ቀናነቱን አትይ፤ እኔ እርሱን አልፈለግሁትም፤ እኔ የምፈርደው ሰዎች እንደሚፈርዱት አይደለም፤ ሰው የውጪ መልክን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።