ኢዮብ 10:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ በእኔ ላይ ያለህን ቅርታ ግለጥልኝ እንጂ አትፍረድብኝ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፤ በምን ላይ እንዳልተስማማን ንገረኝ እንጂ አትፍረድብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ አትፍረድብኝ፥ የምትከራከረኝ ለምን እንደሆነ ንገረኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ ኀጢኣተኛ እንድሆን አታስተምረኝ፤ ለምንስ እንደዚህ ፈረድህብኝ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ አትፍረድብኝ፥ የምትከራከረኝ ለምን እንደ ሆነ ንገረኝ። |
“ኢዮብ ሆይ! ለመሆኑ ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ተከራክሮ ሊረታ የሚችል ይመስልሃልን? ከእኔ ከእግዚአብሔር ጋር የምትከራከር አንተ ስለ ሆንክ፥ እስቲ መልስ ስጥ።”
አንተ ሰዎችን በመቈጣጠር የምትከታተል አምላክ ሆይ፥ እኔ ኃጢአት በመሥራቴ አንተ ምን ተበደልክ? ስለምን ዒላማ አደረግኸኝ? ይህን ያኽል ከባድ ሸክም ሆንኩብህን?