አንተ፥ ወንዶች ልጆችህና አገልጋዮችህ ለጌታህ ለሳኦል ቤተሰብ ምድሪቱን አርሳችሁ ምግብ ይሆናቸው ዘንድ መከሩን አገቡላቸው፤ የጌታህ የልጅ ልጅ መፊቦሼት ግን ዘወትር በገበታዬ የሚቀርብ ተመጋቢ ይሆናል፤” ጺባ ዐሥራ አምስት ወንዶች ልጆችና ኻያ አገልጋዮች ነበሩት።
ኤርምያስ 52:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሚኖርበት ዘመን ሁሉ በየቀኑ ለማናቸውም ለሚያስፈልገው ነገር ያውለው ዘንድ የዘወትር አበል ይሰጠው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎንም ንጉሥ፣ ዮአኪን እስኪሞት ድረስ፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሳያቋርጥ በየዕለቱ ቀለቡን ይሰጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እርሱም ቀለብ የባቢሎን ንጉሥ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ፥ እስኪሞት ድረስ፥ በየዕለቱ የሚያስፍልገውን የዘወትር ቀለብ ይሰጠው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎንም ንጉሥ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ እስኪሞት ድረስ የዘወትር ድርጎ ዕለት ዕለት ይሰጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎንም ንጉሥ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ እስኪሞት ድረስ የዘወትር ቀለብ ዕለት ዕለት ይሰጠው ነበር። |
አንተ፥ ወንዶች ልጆችህና አገልጋዮችህ ለጌታህ ለሳኦል ቤተሰብ ምድሪቱን አርሳችሁ ምግብ ይሆናቸው ዘንድ መከሩን አገቡላቸው፤ የጌታህ የልጅ ልጅ መፊቦሼት ግን ዘወትር በገበታዬ የሚቀርብ ተመጋቢ ይሆናል፤” ጺባ ዐሥራ አምስት ወንዶች ልጆችና ኻያ አገልጋዮች ነበሩት።
እኔም መልስ ሳልሰጥ ናቡዛርዳን “እንግዲያውስ የሳፋን የልጅ ልጅ ወደ ሆነው ወደ አሒቃም ልጅ ወደ ገዳልያ ዘንድ ሂድ፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ገዳልያን የይሁዳ ከተሞች ገዢ አድርጎ ሾሞታል፤ ስለዚህም ከእርሱ ጋር ሆነህ በሕዝቡ መካከል መኖር ትችላለህ፤ ወይም ይጠቅመኛል ብለህ ወደምታስበው ስፍራ ሁሉ መሄድ ትችላለህ።” ከዚያም በኋላ ልዩ ስጦታና ይዤው የምሄደውንም ስንቅ ሰጥቶ አሰናበተኝ።