ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነው አንድ ባለሥልጣን፥ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ የነበሩትን አምስቱን የንጉሥ አማካሪዎች፥ የአገሩን ሕዝብ ለወታደርነት ይመለምል የነበረውን መኰንንና ሌሎችንም ሥልሳ ሰዎችን ወሰደ፤
ኤርምያስ 52:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነ አንድ ባለ ሥልጣንና እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ ውስጥ የተገኙትን ሰባቱን የንጉሡን አማካሪዎች፥ የወታደራዊ ጉዳዮች ጸሐፊ የነበረውን የጦር አዛዡን ረዳትና ሌሎችንም ሥልሳ ታላላቅ ሰዎች ወሰደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከተማው ውስጥ ከቀሩትም ሕዝብ፣ የተዋጊዎቹ ኀላፊ የነበረውን መኰንን፣ ሰባቱን የንጉሡን አማካሪዎች ከአገሬው ሕዝብ ወታደር የሚመለምለውን መኰንን ጸሓፊና በከተማው ውስጥ የተገኙትን ሌሎች ስድሳ ሰዎች ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከከተማይቱም በወታደሮች ላይ ተሾሞ ከነበረው አንዱን አዛዥ፥ በከተማይቱም ውስጥ ከተገኙት የንጉሡ አማካሪዎች ሰባቱን ሰዎች፥ የአገሩንም ሕዝብ ለጦርነት የሚመለምለውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከተማይቱም ከተገኙት ከአገሩ ሕዝብ ስልሳ ሰዎች ወሰደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከከተማዪቱም በሰልፈኞች ላይ ተሾመው ከነበሩት አንዱን ጃንደረባ፥ በከተማዪቱም ከሚገኙት በንጉሡ ፊት ከሚቆሙት ሰባቱን ሰዎች፥ የሀገሩን ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከተማዪቱም ከተገኙት የሀገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎችን ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከተማይቱም በሰልፈኞች ላይ ተሾመው ከነበሩት አንዱን ጃንደረባ፥ በከተማይቱም ከሚገኙት በንጉሡ ፊት ከሚቆሙት ሰባቱን ሰዎች፥ የአገሩንም ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከተማይቱም ከተገኙት ከአገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎች ወሰደ። |
ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነው አንድ ባለሥልጣን፥ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ የነበሩትን አምስቱን የንጉሥ አማካሪዎች፥ የአገሩን ሕዝብ ለወታደርነት ይመለምል የነበረውን መኰንንና ሌሎችንም ሥልሳ ሰዎችን ወሰደ፤
ዘወትር የሚያማክሩትም ካርሸና፥ ሼታር፥ አድማታ፥ ታርሺሽ፥ ሜሬስ፥ ማርሰናና መሙካን ተብለው የሚጠሩ በመንግሥቱ አመራር ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ሰባቱ የፋርስና የሜዶን ሹማምንት ነበሩ።
ሕዝቡም ለማዳመጥ በሚችልበት ሁኔታ ባሮክ እኔ የነገርኩትን በብራና ጽፎት የነበረውን ቃል ሁሉ አነበበላቸው። በቤተ መቅደስ ውስጥ ይህን ያደረገው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ክፍል በኩል ዘልቆ ነበር፤ ክፍሉም የሚገኘው ወደ ቤተ መቅደስ ከሚያስገባው አዲስ የቅጽር በር አጠገብ በላይኛው አደባባይ በኩል አለፍ ብሎ ነበር።