ኤርምያስ 51:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እረኛውንና መንጋውን፥ ገበሬውንና ጥማድ በሬዎቹን፥ ገዢዎችንና ታላላቅ ባለሥልጣኖችን ለማጥፋት መሣሪያ አደረግሁሽ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንቺ እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፣ በአንቺ ገበሬውንና በሬውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺ ገዦችንና ባለሥልጣኖችን እሰባብራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማጁን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ገዢዎችንና ሹማምቶችን አሰባብራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እበትናለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማዱን እበትናለሁ፤ በአንቺም አለቆችንና መሳፍንትን እበትናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም አራሹንና ጥማጁን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም አለቆችንና ሹማምቶችን አሰባብራለሁ። |
መሳፍንትዋ፥ የጥበብ ሰዎችዋ፥ መሪዎችዋ፥ የጦር አዛዦችዋና ወታደሮችዋ ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይተኛሉ፤ እስከ ዘለዓለም አይነቁም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ንጉሡ ነኝ፤ ስሜም የሠራዊት አምላክ ነው።