ኤርምያስ 50:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ ሕዝብ ከሰሜን እየመጣ ነው፥ ኀያል ሕዝብና ብዙ ነገሥታት ከምድር ዳርቻ እየተንቀሳቀሱ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ ሰራዊት ከሰሜን ይመጣል፤ አንድ ኀያል መንግሥትና ብዙ ነገሥታት፣ ከምድር ዳርቻ ተነሣሥተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል፤ ታላቅ ሕዝብና ብዙ ነገሥታትም ከምድር ዳርቻ ይነሣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል፤ ታላቅ ሕዝብና ብዙ ነገሥታትም ከምድር ዳርቻ ይነሣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል ታላቅ ሕዝብና ብዙ ነገሥታትም ከምድር ዳርቻ ይነሣሉ። |
እኔ ከወደ ሰሜን የተባበሩ ሕዝቦች በባቢሎን ላይ እንዲዘምቱ አነሣሣለሁ፤ በእርስዋም ላይ አደጋ ይጥሉባታል፤ ከዚያም ትያዛለች፤ የእነርሱም ቀስቶች ተወርውረው ዒላማቸውን እንደማይስቱ እንደ ሠለጠኑ ወታደሮች ቀስቶች ናቸው።
የእግዚአብሔር ዓላማ ስለ ቤተ መቅደሱ የበቀል ዕርምጃ ለመውሰድ ስለ ሆነ ባቢሎንን ለማጥፋት የሜዶንን ነገሥታት አነሣሥቶአል፤ ስለዚህ ፍላጻችሁን ሳሉ! ጋሻችሁንም አንሡ!
አውሬውና ያየሃቸው ዐሥር ቀንዶች አመንዝራይቱን ይጠላሉ፤ ወደ ጥፋት ያደርሱአታል፤ ራቁትዋን ያስቀሩአታል፤ ሥጋዋን ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል፤