እንዲህም እያሉ ስለ አንቺ ሙሾ ያወጣሉ፤ ‘በባሕር ጠረፍ ያሉ አገሮችን ያሸበራችሁ፥ በባሕር ላይ ኀያል የነበርሽ ዝነኛይቱ ከተማ ሆይ! እንዴት ከባሕር ጠፋሽ?
ኤርምያስ 50:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዓለምን ሕዝብ እንደ መዶሻ ታደቅ የነበረችው ባቢሎን እርስዋ ራስዋ ደቃለች፤ በዚያች አገር ላይ የደረሰው በሕዝቦች ዘንድ ምንኛ አስደንጋጭ ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድር ሁሉ መዶሻ፣ እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ ደቀቀ! በሕዝቦች መካከል፣ ባቢሎን እንዴት ባድማ ሆነች! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ደቀቀ እንዴትስ ተሰበረ! ባቢሎንስ በአሕዛብ መካከል እንዴት መሣቀቅያ ሆነች! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድርን ሁሉ የምትፈጫት መዶሻ እንዴት ደቀቀች! እንዴትስ ተሰበረች! ባቢሎንስ በአሕዛብ መካከል እንዴት ባድማ ሆነች! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ደቀቀ እንዴትስ ተሰበረ! ባቢሎንስ በአሕዛብ መካከል እንዴት ባድማ ሆነች! |
እንዲህም እያሉ ስለ አንቺ ሙሾ ያወጣሉ፤ ‘በባሕር ጠረፍ ያሉ አገሮችን ያሸበራችሁ፥ በባሕር ላይ ኀያል የነበርሽ ዝነኛይቱ ከተማ ሆይ! እንዴት ከባሕር ጠፋሽ?
“ቀጭን ልብስና ሐምራዊ ልብስ ቀይ ልብስም ትለብስ የነበረች፥ በወርቅና በከበረ ድንጋይ በዕንቊም ታሸበርቅ የነበረች፤ ታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት!