ኤርምያስ 5:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሠቃቂና አስደንጋጭ የሆነ ነገር በዚህች ምድር ላይ ተፈጽሞአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ነገር በምድሪቱ ላይ ሆኗል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሠቃቂና አስደንጋጭ ነገር በምድሪቱ ላይ ሆኖአል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምትሰቀጥጥና የምታስደነግጥ ነገር በምድር ላይ ሆናለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር በምድር ላይ ሆናለች፥ |
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን የመሰለ ነገር በሕዝቦች መካከል ተሰምቶ እንደ ሆነ ጠይቁ፤ የተለዩ የእስራኤል ሕዝብ በጣም አጸያፊ የሆነ ነገር አድርገዋል።
ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚገኙ ነቢያትም ከዚህ የባሰ ክፋት ሲያደርጉ አይቼአለሁ፤ እነርሱ ያመነዝራሉ፤ ሐሰትም ይናገራሉ፤ ሰዎችን ለክፉ ሥራ ያነሣሣሉ፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ ከክፉ ሥራቸው አይመለሱም። ስለዚህ እነርሱ በእኔ ዘንድ እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ሕዝብ የከፉ ናቸው።