“ለጻድቁ ለእርሱ ክብር ይሁን!” የሚል መዝሙር ከዓለም ዳርቻ ይሰማል። እኔ ግን እጅግ በመክሳት ስለ መነመንኩ ወዮልኝ! ከዳተኞች በከዳተኝነታቸው ጸንተዋል፤ ከዳተኛነታቸውም እየባሰ ሄዶአል።
ኤርምያስ 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ፈጽሞ ከድተውኛል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት፣ ፈጽመው ከድተውኛል፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ አታለዋል ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ ወንጅለዋል” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ ወንጅለዋል ይላል እግዚአብሔር። |
“ለጻድቁ ለእርሱ ክብር ይሁን!” የሚል መዝሙር ከዓለም ዳርቻ ይሰማል። እኔ ግን እጅግ በመክሳት ስለ መነመንኩ ወዮልኝ! ከዳተኞች በከዳተኝነታቸው ጸንተዋል፤ ከዳተኛነታቸውም እየባሰ ሄዶአል።
እኔ የምናገረውን አትሰሙም፤ ለማወቅም አትፈልጉም፤ ከጥንት ጀምሮ ጆሮአችሁ የተደፈነ ነው፤ ይህም የሆነው እናንተ በጣም ከዳተኞች መሆናችሁንና ከተወለዳችሁ ጀምሮ ዐመፀኞች ተብላችሁ መጠራታችሁን ዐውቃለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ከአንተ ጋር በምከራከርበት ጊዜ ሁሉ አንተ ትክክለኛ ነህ፤ አሁን ግን ስለ ትክክለኛ ፍርድ ጥያቄ አለኝ፤ የኃጢአተኛ ሕይወት የተቃና የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? አታላዮችስ ሁሉ ነገር የሚሳካላቸው ስለምንድን ነው?
የሕዝቤን የወይን ተክል ቈራርጠው የሚያበላሹ ጠላቶችን እልካለሁ፤ ነገር ግን ሥር መሠረታቸውን እንዲያጠፉ አላደርግም፤ ቅርንጫፎቹ የእኔ ባለመሆናቸው፥ ቈርጠው እንዲጥሉአቸው አዛለሁ።
ሕዝቤ እምነተ ቢሶችና አታላዮች ስለ ሆኑ፥ ከእነርሱ ተለይቼ በምድረ በዳ ውስጥ የምኖርበት የመንገደኞች ማደሪያ ቦታ ባገኝ፥ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር!
እነርሱ ራሳቸው ጣዖት አምላኪዎች ስለ ሆኑ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልተገኙም። ልጆቻቸውም እንደ ጣዖት ልጆች ተቆጥረዋል፤ ስለዚህ በዚህ ወር መባቻ እነርሱም ምድራቸውም አብረው ይጠፋሉ።