ከተሞቻቸውን ደመሰሱ፤ ለም በሆነው እርሻ ውስጥ በሚያልፉበትም ጊዜ እያንዳንዱ እስራኤላዊ አንዳንድ ድንጋይ ይወረውርበት ስለ ነበር በመጨረሻ እርሻዎቹ ሁሉ በድንጋይ ተሸፈኑ፤ ምንጮቻቸውን ደፈኑ፤ የፍራፍሬ ዛፎቻቸውንም ሁሉ ቈረጡ፤ በመጨረሻም የአገሪቱ ዋና ከተማ የነበረችው ቂርሔሬስ ብቻ ቀረች፤ እርስዋንም ድንጋይ የሚያወነጭፉ ጦረኞች ከበው አደጋ ጣሉባት።
ኤርምያስ 48:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሞአብ ዋይ፥ ዋይ እልላታለሁ፤ ለሞአባውያን ሁሉ ድምፄን ከፍ ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ፥ ለቂርሔሬስ ሰዎች የሐዘን ለቅሶ አለቅሳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፤ ለሞዓብ ምድር ሁሉ ዋይ እላለሁ፤ ለቂርሔሬስ ሰዎችም የልቅሶ ድምፅ አሰማለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ ለሞዓብም ሁሉ እጮኻለሁ፤ ለቂርሔሬስ ሰዎች አለቅሳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰለዚህ ለሞአብ አለቅሳለሁ፤ ለሞአብም ሁሉ እጮኻለሁ፤ ለቂርሔሬስ ሰዎች አለቅሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ ለሞዓብም ሁሉ እጮኻለሁ፥ ለቂርሔሬስ ሰዎች አለቅሳለሁ። |
ከተሞቻቸውን ደመሰሱ፤ ለም በሆነው እርሻ ውስጥ በሚያልፉበትም ጊዜ እያንዳንዱ እስራኤላዊ አንዳንድ ድንጋይ ይወረውርበት ስለ ነበር በመጨረሻ እርሻዎቹ ሁሉ በድንጋይ ተሸፈኑ፤ ምንጮቻቸውን ደፈኑ፤ የፍራፍሬ ዛፎቻቸውንም ሁሉ ቈረጡ፤ በመጨረሻም የአገሪቱ ዋና ከተማ የነበረችው ቂርሔሬስ ብቻ ቀረች፤ እርስዋንም ድንጋይ የሚያወነጭፉ ጦረኞች ከበው አደጋ ጣሉባት።
ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።