ነቢዩ ኤርምያስም ለንጉሥ ኢዮስያስ የለቅሶ ሙሾ አወጣለት፤ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች አልቃሾች ኢዮስያስን በማስታወስ፥ በሚያለቅሱበት ጊዜ በዚሁ በነቢዩ ኤርምያስ የለቅሶ ሙሾ ማልቀስ በእስራኤል አገር የተለመደ ሆነ፤ ይህም የለቅሶ ሙሾ የእስራኤልን የለቅሶ ሰቆቃ በያዘ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።
ኤርምያስ 4:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰልፍ ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ፥ የጦርነት ድምፅ ሲያስገመግም፥ የጥሩምባም ድምፅ ሲያስተጋባ የምሰማው እስከ መቼ ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ መቼ የጦርነት ዐርማ እመለከታለሁ? እስከ መቼስ የመለከት ድምፅ እሰማለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓላማውን የምመለከት፥ የመለከቱንስ ድምፅ የምሰማ እስከ መቼ ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚሸሹትን የምመለከት፥ የመለከቱንስ ድምፅ የምሰማ እስከ መቼ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓላማውን የምመለከት፥ የመለከቱንስ ድምፅ የምሰማ እስከ መቼ ነው? |
ነቢዩ ኤርምያስም ለንጉሥ ኢዮስያስ የለቅሶ ሙሾ አወጣለት፤ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች አልቃሾች ኢዮስያስን በማስታወስ፥ በሚያለቅሱበት ጊዜ በዚሁ በነቢዩ ኤርምያስ የለቅሶ ሙሾ ማልቀስ በእስራኤል አገር የተለመደ ሆነ፤ ይህም የለቅሶ ሙሾ የእስራኤልን የለቅሶ ሰቆቃ በያዘ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።
የጸደይ ወራት በደረሰ ጊዜ ንጉሥ ናቡከደነፆር ኢኮንያንን እስረኛ አድርጎ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ የቤተ መቅደሱንም ሀብት ዘርፎ ወሰደ፤ ከዚህ በኋላ የኢኮንያን አጎት የሆነውን ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።
ስለዚህ የባቢሎን ንጉሥ በእነርሱ ላይ አደጋ እንዲጥል እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ንጉሡም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን እንኳ ሳይቀር፥ በይሁዳ የሚገኙትን ወጣቶች ወንዶችን ሁሉ በሰይፍ ፈጀ፤ እግዚአብሔር ለናቡከደነፆር አሳልፎ ስለ ሰጣቸውም ወጣት ወይም ሽማግሌ፥ ወንድ ወይም ሴት ማንንም ሳይለይ፥ ሁሉንም ያለ ምሕረት አጠፋቸው።
የግብጽ ንጉሥ ኒካዑ ኢዮአሐዝን እስረኛ አድርጎ ወሰደው፤ የይሁዳንም ሕዝብ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚመዝን ብርና ሠላሳ አራት ኪሎ የሚመዝን ወርቅ እንዲገብርለት አደረገ።
ወይ ሥቃይ! ይህን ሁሉ ሥቃይ እንዴት መታገሥ እችላለሁ! ወይ ልቤ! የልቤ አመታት እንዴት ፈጠነ? የጥሩምባ ድምፅና የጦርነት ድምፅ እየሰማሁ፥ ዝም ብዬ መታገሥ አልችልም።
መቅሠፍት በመቅሠፍት ላይ ይደራረባል፤ አገሪቱ በሙሉ ፈራርሳ ጠፍ ሆናለች፤ ድንኳኖቻችን በድንገት ወደሙ፤ መጋረጃዎቻቸውም በቅጽበት ተቀደዱ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን የማያውቁ ሞኞች ሆነዋል፤ ማስተዋል ስለ ጐደላቸው እንደ ሕፃናት የሚታለሉ ናቸው፤ ክፉ ነገር ለመሥራት የተራቀቁ ብልኆች ናቸው፤ መልካም ነገር ማድረግ ግን ከቶ አይሆንላቸውም።”
የብንያም ሕዝብ ሆይ! ሕይወታችሁን ለማትረፍ ሽሹ! ከኢየሩሳሌምም ውጡ! በተቆዓ የጥሩምባ ድምፅ አሰሙ፤ በቤትሀካሬም ለምልክት የሚሆን እሳት አንድዱ! መቅሠፍትና ጥፋት ከሰሜን በኩል ሊመጣ ነው።