ዘግየት ብሎም ንጉሥ ሴዴቅያስ መልእክተኛ ልኮ አስወሰደኝና በቤተ መንግሥቱ በግል ሲያነጋግረኝ “ከእግዚአብሔር የተነገረህ የትንቢት ቃል አለን?” ብሎ ጠየቀኝ። “አዎ፥ አለ!” ብዬ ንግግሬን በመቀጠል “አንተ ለባቢሎን ንጉሥ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አልኩት።
ኤርምያስ 38:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴዴቅያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እንዳትሞት ይህን የተነጋገርነውን ነገር ማንም አይወቅ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴዴቅያስም ኤርምያስን እንዲህ አለው፤ “ስለዚህ ስለ ተነጋገርነው ነገር ማንም አይወቅ፤ አለዚያ ትሞታለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴዴቅያስም ኤርምያስን እንዲህ አለው፦ “እነዚህንም ቃላት ማንም አይወቅ፥ አንተም አትሞትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴዴቅያስም ኤርምያስን እንዲህ አለው፥ “ይህን ቃል ማንም አይወቅ፥ አንተም አትሞትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴዴቅያስም ኤርምያስን እንዲህ አለው፦ ይህም ቃል ማንም አይወቅ፥ አንተም አትሞትም። |
ዘግየት ብሎም ንጉሥ ሴዴቅያስ መልእክተኛ ልኮ አስወሰደኝና በቤተ መንግሥቱ በግል ሲያነጋግረኝ “ከእግዚአብሔር የተነገረህ የትንቢት ቃል አለን?” ብሎ ጠየቀኝ። “አዎ፥ አለ!” ብዬ ንግግሬን በመቀጠል “አንተ ለባቢሎን ንጉሥ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አልኩት።
በተጨማሪም እንዲህ አልኩት፦ “ሚስቶችህና ልጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎናውያን ይወሰዳሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ ተይዘህ እስረኛ ትሆናለህ፤ ከእነርሱ እጅ ከቶ አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ተቃጥላ ትወድማለች።”
ባለ ሥልጣኖቹ እኔ ከአንተ ጋር መነጋገሬን የሰሙ እንደ ሆነ መጥተው ምን እንደ ተባባልን ይጠይቁሃል፤ ሁሉን ነገር ባትነግራቸው እንገድልሃለን ብለው ያስፈራሩሃል፤