ኤርምያስ 38:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅህን ለመስጠት እምቢ ብትል ግን እግዚአብሔር ለእኔ የገለጠልኝ ራእይ አለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጅህን ለመስጠት እንቢ ብትል ግን፣ እግዚአብሔር የገለጠልኝ ነገር ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመውጣት እንቢ ብትል ግን፥ ጌታ ያሳየኝ ነገር ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትወጣ ዘንድ እንቢ ብትል ግን፥ እግዚአብሔር ያሳየኝ ቃል ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትወጣ ዘንድ እንቢ ብትል ግን፥ እግዚአብሔር ያሳየኝ ቃል ይህ ነው። |
ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ በጥንቃቄ ልታረጋግጡ ይገባል፤ ይኸውም እኔን ብትገድሉኝ፥ እናንተና የዚህ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ሁሉ ንጹሕ ሰው በመግደላችሁ በደለኞች ሆናችሁ ትገኛላችሁ፤ ይህን ማስጠንቀቂያ እንድሰጣችሁ ወደ እናንተ የላከኝ በእርግጥ ራሱ እግዚአብሔር ነው።”
እኔም እንዲህ አልኩት፦ “አይዞህ! ለእነርሱ ተላልፈህ አትሰጥም፤ እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ፤ ለአንተም መልካም ነገር ይሆንልሃል፤ ሕይወትህም ከጥፋት ትድናለች።
ይኸውም በይሁዳ ቤተ መንግሥት የቀሩት ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎናውያን ባለ ሥልጣኖች ተወስደው በሚሄዱበት ጊዜ እንዲህ ይሉሃል፦ ‘የቅርብ ወዳጆችህ አስተውሃል፤ እነርሱም በአንተ ላይ ሠልጥነውብሃል፤ አሁን ግን እግርህ ማጥ ውስጥ ስለ ገባ ጥለውህ ሄደዋል።’ ”
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
‘ባላቅ በቤተ መንግሥቱ ያለውን ብርና ወርቅ ሁሉ ቢሰጠኝ እንኳ በራሴ ፈቃድ ደግ ወይም ክፉ ነገር አደርግ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል መተላለፍ አልችልም፤ የምናገረው እግዚአብሔር እንድናገር የነገረኝን ነገር ብቻ ነው’ ብዬ ነግሬአቸው አልነበረምን?”
ነገር ግን አይሁድ በተቃወሙትና በሰደቡት ጊዜ የልብሱን ትቢያ አራግፎ “እንግዲህ ቢፈረድባችሁ በራሳችሁ ጥፋት ነው! እኔ ኀላፊነት የለብኝም፤ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ!” አላቸው።
ያንን የሚናገረውን አንቀበልም እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ እግዚአብሔር በሰው አማካይነት ከምድር ሲናገራቸው አንሰማም ያሉት ካላመለጡ፥ ታዲያ እኛ ከሰማይ የሚናገረንን ባንቀበል እንዴት እናመልጣለን!