ኤርምያስ 36:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እየነገርኩት ባሮክ የጻፈውን የብራና ጥቅል ንጉሥ ኢዮአቄም ካቃጠለው በኋላ ሌላ የሚጠቀለል ብራና ወስጄ የቀድሞውን ቃል እንደገና እንድጽፈው እግዚአብሔር አዘዘኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ፣ ባሮክ ከኤርምያስ አፍ ተቀብሎ የጻፈው ቃል ያለበትን ብራና ካቃጠለ በኋላ፤ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ኤርምያስ ለባሮክ እየነገረው የጻፈውን ቃላት የያዘውን ክርታስ ካቃጠለ በኋላ የጌታ ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ ባሮክ ከኤርምያስ አፍ የጻፈው ቃል ያለበትን ክርታስ ካቃጠለ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ክርስታሱንና ባሮክ ከኤርምያስ አፍ የጻፈውን ቃል ካቃጠለ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ |
ይሁዲም ሦስት ወይም አራት ዐምድ ያኽል አንብቦ በጨረሰ ቊጥር ንጉሡ የተነበበለትን ብራና በመቊረጫ ቈራርጦ እሳት ውስጥ ይጥለው ነበር፤ በዚህም ዐይነት የብራናውን ጥቅል በሙሉ አቃጠለው።