ኤርምያስ 24:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “ኤርምያስ ሆይ! ይህ የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም “እነሆ የበለስ ፍሬዎችን አያለሁ፤ ጥሩዎቹ ፍሬዎች እጅግ የተዋቡ ናቸው፤ መጥፎዎቹ ፍሬዎች ደግሞ ለምግብነት ደስ የማይሉና እጅግ የተበላሹ ናቸው” ስል መለስኩለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም፣ “ኤርምያስ ሆይ፤ የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፣ “በለስን አያለሁ፤ ጥሩ የሆነው እጅግ መልካም ነው፤ የተበላሸው ግን እጅግ መጥፎ በመሆኑ ሊበላ የማይችል ነው” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም፦ “ኤርምያስ ሆይ! የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “በለስን አያለሁ፤ እጅግ መልካም የሆነ መልካም በለስ፥ ከክፋቱም የተነሣ ሊበላ የማይችል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው” አልሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም፥ “ኤርምያስ ሆይ! የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “በለስን አያለሁ፤ እጅግ መልካም የሆነ መልካም በለስ፥ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፦ ኤርምያስ ሆይ፥ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ በለስን አያለሁ፥ እጅግ መልካም የሆነ መልካም በለስ፥ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው አልሁ። |
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ በእነርሱ ላይ ጦርነትን፥ ራብንና ቸነፈርን ላመጣባቸው ነው፤ ከመበላሸቱ የተነሣ ሊበሉት እንደማይቻል የበለስ ዛፍ ፍሬ አደርጋቸዋለሁ፤
እርሱም “አሞጽ ሆይ! የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀኝ። እኔም “ቱምቢ ነው” አልኩ። ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “በቱምቢ ተስተካክሎ እንዳልተሠራ ቅጽር ሕዝቤ እስራኤል ጠማሞች ሆነው ስለ ተገኙ ይህ ቱምቢ የእስራኤልን ጠማማነት ማሳያ ምሳሌ ነው፤ ሳልቀጣቸውም አላልፍም።
እግዚአብሔርም “ይህ የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “የጐመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት አያለሁ” አልኩት። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ “የሕዝቤ የእስራኤል ፍጻሜ ደርሶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ እነርሱን ከመቅጣት አልመለስም።
“ይህ የምታየው ምንድን ነው?” ብሎም ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩለት፦ “ሰባት መብራቶች ያሉበት አንድ የወርቅ መቅረዝ አያለሁ፤ በአናቱም ላይ የዘይት ማሰሮ አለ፤ ሰባቱም መብራቶች የክር ማስተላለፊያ ቧንቧ አላቸው።
መልአኩም “ምን ታያለህ?” ብሎ ጠየቀኝ፤ እኔም “ርዝመቱ ዐሥር ሜትር፤ ስፋቱም አምስት ሜትር የሆነ፥ አንድ የተጠቀለለ የብራና መጽሐፍ በአየር ላይ ሲበር አያለሁ” አልኩት።
በቀድሞ ዘመን በእስራኤል ዘንድ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲፈልግ ወደ ባለ ራእዩ እንሂድ ይል ነበር፤ አሁን ነቢይ የሚባለው በዚያን ጊዜ ባለ ራእይ ይባል ነበር።