ኤርምያስ 21:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ቃሉን ስለ ነገረኝ ወደ እኔ ተልከው የመጡትን ሰዎች ለሴዴቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት አልኳቸው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ለሴዴቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም እንዲህ አላቸው፦ “ሴዴቅያስን እንዲህ በሉት፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም እንዲህ አላቸው፥ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን እንዲህ በሉት፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም እንዲህ አላቸው፦ ሴዴቅያስን እንዲህ በሉት፦ |
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከነሠራዊቱ ከተማይቱን ለመውጋት በመክበብ ላይ ይገኛል፤ ስለዚህ ምናልባት በረድኤት ከእኛ ጋር ሆኖ ድንቅ ሥራውን በመግለጥ ናቡከደነፆርን እንዲመለስ ያደርግልን እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ጠይቅልን።”
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፤ ‘ሴዴቅያስ ሆ! ከቅጽርህ በስተውጪ በኩል ከበባ ያደረጉብህን የባቢሎንን ንጉሥና ባቢሎናውያንን የምትዋጋበት የጦር መሣሪያ አንተን ተመልሶ እንዲያጠቃ አደርጋለሁ፤ የጦር መሣሪያውንም በከተማይቱ መካከል እንዲከመር አደርጋለሁ።
ንጉሥ ሴዴቅያስ እኔን በዚያ እስረኛ አድርጎ ያስቀመጠኝና የከሰሰኝ እግዚአብሔር የተናገረኝን የትንቢት ቃል ለእርሱ በማሳወቄ ሲሆን፥ እርሱም እንዲህ የሚል ነበር፥ “የባቢሎን ንጉሥ ይህችን ከተማ በኀይል እንዲይዝ ልፈቅድለት ነው፤